እኛ ሀገር ከጦርነት በኃላ የማይድን በሽታ አለ። | ይፍቱስራ ምትኩ | hareg podcast
Update: 2025-04-11
Description
ይፍቱስራ ምትኩ ከአዲሱ ትውልድ ሴት ፀሐፍት መሐል ቀድመን ከምንጠራቸው ናት ። ሁለት መፅሀፍትን በተወሰኑ አመታት ልዩነት ውስጥ አንባቢዎች ጋር አድርሳለች ። በመፅሀፎቿ የአተራረክ ስልት የቋንቋ አጠቃቀምና ግጥማዊ ባህሪያቸው ከሁሉ ለይተን ይፍቱስራ የጻፈችው ነው ለማለት የሚያስደፍር የራሷን መንገድ እየፈጠረች ነው ። በሁለቱ መፅሀፎቿ ውብ በኾነ መንገድ የማህበረሰብ አረዳድና ስርዓት ፣ ቤተሰብ ፣ ጦርነትና ሌሎች ሐሳቦች ተዳሰዋል ። ከይፍቱስራ ጋር ስነ ፅሁፍና ሴቶች በተመለከቱ ርዕሶች በኩል ስለስራዎቿና ተያያዥ ሐሳቦች ላይ አውግተናል ።
Comments
In Channel